About BOLE

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ስልጠና ኤጀንሲ ለህብረተሰቡ የቴክኒከና ሙያ ትምህርትና ስልጠናን ተደራሽ ለማድረግ በቦሌ ክፍለ ከተማ ደረጃውን የጠበቀ ተቋም በመገንባት የህብረተሰቡንና ኢንዱስትሪውን ፍላጎት ለማሟላት በ2007 ዓ.ም ቦሌ ህዳሴ ቴከኒክና ያ ተቋም ተመሰረተ፡፡ ተቋሙ በ2007 ዓ.ም 36 በወለል ንጣፍ ኣጭር ሰልጣኞችን በመቀበል ስራውን የጀመረ ሲሆን በ2008 ዓ.ም እስታንዳርዱን የጠበቀ ሶስት የጋርመንት ወርክሾፕ ተገንብተው ሰኔ 2008 ዓ.ም ክቡር ከንቲባው አቶ ድሪባ ኩማ በተገኙበት ከቦሌ ህዳሴ ቴክኒክና ሙያ ተቋም ወደ ቦሌ ማኑፋከቸሪንግ ኮሌጅ የስም ቅያሬ በማድረግ ከተቋምነት ወደ ኮሌጅነት እንዲያድግ ተደርጓል፡፡ ኮሌጁ በዋናነት ቦሌ ለሚ ኢንዱስትሪ ፓርክን መሰረት አድርጎ በጋርመንት ሙያ ዘርፍ ላይ ትኩረት ሰጥቶ እንዲሰራና ለፓርኩን ብቁ የሆነ የሰው ኃይል ፍላጎት ለማርካት ታስቦ የተመሰረተ ቢሆንም ከዚህ በተጨማሪም በኮንስትራክሽን በምግብ ዝግጅት ፤ በአዉቶሞቲቬ ቴክኖሎጂ፣ በአይሲቲ፣ በአካዉንቲንግ፣ በብረታብረት ስራና በእንጨት ስራ ዘርፎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡ ኮሌጁ በአንድ ዋና ካምፓስ የተመሰረተና ሥራ የጀመረ ሲሆን ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ የቦሌ ቴ/ት/ስ/ተቋምን ማለትንም የመገናኛ ካምፓስ እንደ ቅርንጫፍ በማድረግ እየሰራ ይገኛል፡፡ እስካሁን ባለው ኮሌጁ በኢንዱስትሪ እና በአገልግሎት ዘርፍ ተሰማርተው መሥራት የሚችሉ በመለስተኛና በመካከለኛ ደረጃ የሰለጠኑ ሙያተኞችን በማፍራት ወደ ኢንዱስትሪ መር ኢኮኖሚ ለመሸጋገር የሚደረገዉን ጥረት በማገዝ የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ ባደረገዉ እጅግ ፈታኝ በሆኑ የአመለካከትና የግብኣት ችግሮችን በመቋቋም ኢኮኖሚው በሚፈልገው ልክ ብቃት ያላቸው በራሳቸው የሚተማመኑና ቴከኖሎጂን የሚቀዱ፤ ተወዳዳሪ የሆኑ ምርትና አገልግሎቶችን በማቅረብ ሀብት ማፍራት የቻሉ ስራ ፈጣሪ ዜጎችን ማፍራት ተችሏል፡፡ በመሆኑም ኮሌጁ የዘርፉ አንዱ ተልእኮ ሆነውን የቴከኖሎጂ አቅም በመገንባት የኢንዳስትሪዎች ተወዳዳሪነት ማረጋገጥና በሀገር ደርጃ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ለማስቻል በቴክኖሎጂ ሽግግር ረገድም አዋጭ የሆኑ ቴክኖሎጂዎችን በመቅዳት ለጥቃቅንና አነስተኛ ኢንተርፕራይዞዎችና አንቀሳቃሾች በማሸጋገር እንዲሁም ውጤትን መሰረት ያደረገ ድጋፍ በመስጠትና በማብቃት በኩል ከፍተኛ ጥረት በማድረግ ላይ ነው፡፡ ኮሌጁ በየደረጃው የቴክኖሎጂ፤ የከህሎት እና የምርምር ስራዎችና ውጤቶች ውድድር አውደ ርዕይ፣ ፓናል ውይይቶችን እና ሲምፖዚየሞችን በማካሄድ በአሠልጣኝ፣ በሠልጣኝ በኢንተርፕራይዝ አንቀሳቃሾች እና በሌሎች ምሁራን ዘንድ የውድድርና የተነሳሽነት መንፈስ መፍጠር፡ በዘርፍ ያሉ የተለያዩ ባለሙያዎች የምርምር ስራን እንደ አንዱ ቁልፍ የስራ ድርሻቸው እንዲይዙት በማድረግ ለምርምር ስራዎቻቸው እውቅና መስጠት ብሎም በእውቀቱ፣ በክህሎቱና በሁለንተናዊ አመለካከት የበቃ ዜጋን ለማፍራት በተጨባጭ ተግባራዊ የሚደረጉ የመፍትሄ እርምጃዎች ለማምጣት ሌት ተቀን በመስራት ላይ ይገኛል፡፡ በአጠቃላይ ኮሌጃችን አመታዊ የሰልጣኝ ቅበላን ከ2008 ዓ.ም እስከ አሁን ድረስ ባለዉ የትምህርትና ስልጠና ዘመን የቅበላው ቁጥር የመጨመር አዝማሚያ እያሳየ የሚገኝ ቢሆንም በአዲሱ የትምህርትና ስልጠና ፍኖተ ካርታው ጥናት ላይ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የመሰናዶ ትምህርት በመቅረቱና አስራኛ ከፍልን ያጠናቀቁ ተማሪዎች አስከ አስራ ሁለተኛ ክፍል ድረስ አንዲቀጥሉ መደረጉ አና በአገር አቀፍ ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ መከሰት በምክንያትነት የተወሰዱ ችግሮች ናቸው፡፡

  • Deans

    Bole Manufacturing College All Adminstratives Photo And Contact Info

    Read more
  • Directorates

    Bole Manufacturing College All Directorates

    Read more
  • All Course

    Bole Manufacturing College Short Term And Long Term Course List

    Read more

bole manufacturing college

For a Bright Future