Bole Manufacturing College All Deans




የኮሌጅ ዋና ዲን

አቶ ኦላና ሙቲ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ዘላቂነት ባለው ፈጣን የኢኮኖሚ ዕድገት ወደፊት ለመቀጠል እንድትችል ከተፈለገ የትኛዎቹንም የልማት ስራዎቻችን በመሠረታዊነትና ዘላቂነት ባለው መልኩ ከሠው ኃብትና ቴከኖሎጂ ልማታችን ጋር አቀናጅተን መተግበር ያስፈልገናል፡፡

የተቋማት አቅም ግንባታ ዋና ዲን

ወ/ሮ ሙሉ ይታየው

የሀገራችንን ህዳሴ ቀጣይነት ለማረጋገጥ ትኩረት በተሰጣቸው ዘርፎች ተፈላው ክህሎት ያለው በዝቅተኛና መካከለኛ ደረጃ የሰለጠነ የሰው ሃይል ማፍራትና ችግር ፈቺ የሆኑ ቴከኖሎጂዎችን ማሸጋገር ላይ መስራት ተገቢ ይሆናል፡፡በመሆኑም ኮሌጃችን ይህንን ተልዕኮ ለማሳካት ባለፉት አመታት አበረታች ስራዎችን ሰርቷል፡፡

የኢንዱስትሪ ኤክስቴንሽን ዋና ዲን

አቶ መላኩ አስፋው

ዓለም በቴክኖሎጂ እድገት ምክንያት በአንድ መንደር በተመሰለችበት በዚህ በ2ኛው ክፍለ ዘመን፣ ለአንድ ሀገር ዕድገት እና ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እንዲሁም ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመፍታት የሀገሪቱን ተጨባጭ ሁኔታ መሰረት ያደረገ ችግር ፈቺ የሠው ኃብት ልማት ተኪ የሌለው ቁልፍ ስራ ነው፡፡

የሰልጣኝ ልማት ዋና ዲን

አቶ መክብብ ተፈሪ

ሀገራችን ፈጣንና ዘላቂነት ያለው የኢኮኖሚ እና ማኅበራዊ ዕድገት ለማረጋገጥ የዕደግትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ነድፋ በመተግበር ላይ ትገኛለች፡፡ የቴ/ሙት/ስ ዘርፍም አገራችን የተያያዘችውን ፈጣን ልማት ዘላቂነት ባለው መልኩ ለማሳደግ እና አገራዊ ራዕያችንን እውን ለማድረግ ብቁ የሰው ኃይል በማቅረብ ረገድ የማይተካ ሚና አለው፡፡

የካምፓስ ምክትል ዲን

አቶ ምትኩ ሃኮንሶ

የሀገራችን የልማት ዕቅዶች ሊሳኩ የሚችሉት የበቃ የሰው ኃይልና ተስማሚ ቴከኖሎጂ ልማቱ በሚያስፈልገው መጠን እና ደረጃ በአግባብ ማቅረብ ስንችል ነው፡፡ ስለዚህም ህብረተሰቡ ከልማቱ ፍትሃዊ ተጠቃሚ መሆን የሚችለው የሙያ ባለቤት በመሆን ልማቱ የሚጠይቀውን ሲያቀርብ ነው፡፡

bole manufacturing college

For a Bright Future