ቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ

  • 09OCT,2024

    የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ

    ቀን መስከረም 30/2017 ዓ/ም የቦሌ ማኑፋክቸሪንግ ኮሌጅ የ2017 በጀት ዓመት መሪ እቅድ ላይ ውይይት አካሄደ። ኮሌጁ የ2016 ዓ/ም በጀት ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም እንደመነሻ በመውሰድ በ2017 በጀት ዓመት ኮሌጁ ሊሰራቸው ባቀዳቸው ስራዎች ላይ አጠቃላይ ከኮሌጁ ማህበረሰብ ጋር በመሆን ውይይት አካሂዶል። የእቅዱን ሰነድ በአጭሩ ለታዳሚዎች ያቀረቡት የኮሌጁ ዋና ዲን የሆኑት አቶ ኦላና ሙቴ ሲሆኑ የእቅዱ ዝርዝር ዓላማዎች የእቅዱ አስፈላጊነት እና የኮሌጁ ተልዕኮ፣ራዕይ እና እሴቶችን በማካተት ሰፋያላ ውይይት ተካሂዷል፡፡ በመጨረሻም የቅሬታ እና ዲሲፒሊን ኮሚቴዎቸን በመምረጥ ውይይቱ ተጠናቋል፡፡

bole manufacturing college

For a Bright Future